ወቅታዊ ጉዳዮች

ወቅታዊ ጉዳዮች

11 Oct: 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የማን ናቸው?

‘ይህ ለቤት መግዣ አላማ የሚሆን ዝግ የቁጠባ ሂሳብ ነው’ ይላል በ40/60 የቤት ባለቤት ለመሆን ከንግድ ባንክ ጋር ውል ፈፅመው የሚገባውን ገንዘብ ገቢ የሚያደርጉበት የቁጠባ ደብተር፡፡ ውሉን ፈፅመው ገንዘባቸውን ያስገቡ እና በየወሩ የተለያየ ቀዳዳዎችን በሕይወታቸው እየተዉ ነገን ተስፋ በማድረግ የቆጠቡ ነዋሪዎች በ2011 ድንገተኛ የመመሪያ ለውጥ በምክትል ከንቲባው ተደረገ፡፡

የመሬት-ቅርምት

11 Sep: የተዳፈነዉ ጩኸት እና የአዲስ አበቤዉ ተስፋአልባ ጉዞ

አፈር ፈጭተን፤የዛሬን አያድርገዉና ሰፊ ሜዳዎቿ ላይ በማይረሱ የልጅነት ጨዋታዎች ቦርቀን፣ተጣልተን፣ታርቀን፣በታሪካዊ መዝናኛዎቿ እሁዳችንን አሳምረን፣ጎረቤት ፍቅር ጠግበን ላደግን ልጆቿ ደግሞ አዲስአበባ በልባችን ልዩ ስፍራ አላ፤ በወርቅ ቀለም ልባችን ላይ ታትማ ትኖራለች፡፡